የተለየ ልጅ
Lindiwe Matshikiza
Meghan Judge

1

አንዲት እርጉዝ ሴትዮ ሆዷን ይዛ አየሁ፡፡

2

የሰፈሬ ሰዎች ሴትዮዋ ከእኛ ጋር እንድትቆይ ፈቀዱላት።

3

በዚያች ሌሊት እርጉዟ ሴትዮ ‹‹ሕፃኑ! ህፃኑ እየመጣ ነው›› በማለት ጮኸች፡፡

4

ሴትዮዋ ዉርንጭላ ወለደች።

5

ሰዎቹ ‹‹ምን እናድርግ›› ሲሉ አሰቡ።

6

ሰዎቹ ሸሹ። ሴትየዋ በበኩሏ ‹‹ይህ ሕፃን የተለየ ነው፡፡ እንዴት ልንከባከበው?›› በማለት አሰበች፡፡

7

በመጨረሻ ልጇን ለመውደድ ወሰነች። ሕፃኑ የተለየ ነበር፤ ነገር ግን ምንም ቢሆን እናቱ ነች፡፡

8

ዉርንጭላው አደገ፤ እናቱም እሱን ለመሸከም ተቸገረች።

9

እናትዮዋ አዘነች። ዉርንጭላው ተናደደ። ዉርንጭላው እናቱን በእርግጫ መታት።

10

11

ዉርንጭላው ተርቦ፣ ደክሞና ብቸኛ ሆኖ ነበር። እንቅልፍም ወሰደው፡፡

12

ዉርንጭላው ከእንቅልፉ ሲነቃ አንድ ሰው ከጎኑ ቆሞ አየ።

13

እንግዳው ሰውዬ ዉርንጭላውን ተሸክሞ ወደ ቤቱ ወሰደው።

14

ዉርንጭላው ሲያድግ ሰውየውን በጀርባው ይሸከመው ጀመር።

15

አንድ ቀን ወደ ኮረብታው ጫፍ ሄደው አረፍ አሉ።

16

ዉርንጭላው ከእንቅልፉ ሲነቃ እንደ በፊቱ ብቻውን ነበር፡፡

17

ዉርንጭላው ተጨነቀ። እናቱን ፍለጋ ሄደ።

18

‹‹ያቺ እናቴ ትሆን?›› ሲል ዉርንጭላው አሰበ።

19

ዉርንጭላውና እናቱ እንደገና አብረው መኖር ጀመሩ። እናቱን ተሸክሞ በመንደራቸው ውስጥ ይዘዋወራል።

20
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
የተለየ ልጅ
Author - Lindiwe Matshikiza
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Meghan Judge
Language - Amharic
Level - First sentences