ባተሌ ባተሌዋ ፀሐይ
Mimi Werna
Joe Werna

ፀሐይ በጠዋት ትወጣለች፤ በምስራቅ በኩል፡፡

ጎህ ሲቀድ ዶሮ ሲጮህ እሰማለሁ።

1

ፀሐይ ወደ መስኮቴ ስትመጣ የቢርና የአኩፓ ጠረን ይጠራኛል።

2

በምሳ ሰዓት ፀሐይ በትምህርት ቤታችን ከዛፍ ጀርባ ትሄዳለች።

ከዚያም በመጫወቻ ስፍራው መካከል ካለው ገንዳ ውስጥ ትደርሳለች፡፡

3

ፀሐይ ከጭንቅላቴ በላይ ትቆማለች። ጥላዬም ከጎኔ ይቆማል።

ከጓደኞቼ ጋር የጥላ ጨዋታ እጫወታለሁ።

4

የእኔ ጥላ ረጅም ይሆናል፤ ከዚያም ትንሽ ይሆናል፡፡ ተከትለነው እንሮጣለን፡፡

የእኔ ጥላ ረጅም ይሆናል፤ ከዚያም ትንሽ ይሆናል፡፡ ተከትለነው እንሮጣለን፡፡

5

እኔ እቆማለሁ፤ ጓደኞቼ ይቆማሉ፡፡ ጥላዎቻችን ሲወዛወዙ እናያለን።

ሲደክመን ወደ ክፍል እንመለሳለን። ከትምህርት በኋላ ወደ ቤት እንሄዳለን፡፡

6

ፀሐይ ታዛጋለች።

ፀሐይ በስተምዕራብ በቀስታ ስትጠልቅ አያታለሁ። ጥላዬን ግድግዳ ላይ አየዋለሁ።

የመኝታ ሰዓት እየደረሰ ነው፡፡

7

ፀሐይ ከደመናው ጀርባ ትጠልቃለች።

አልጋዬ ላይ ተኝቼ ፀሐይ ሩቅ ስትጓዝ በህልሜ አያለሁ።

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ባተሌ ባተሌዋ ፀሐይ
Author - Mimi Werna
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Joe Werna
Language - Amharic
Level - First sentences