ፍየል፣ ውሻና ላም
Fabian Wakholi
Marleen Visser

ፍየል፣ ውሻና ላም ጥሩ ጓደኛሞች ነበሩ፡፡ አንድ ቀን በታክሲ ተሳፍረው ለሽርሽር ሄዱ፡፡

1

በጉዟቸው መጨረሻ ላይ ደረሱ፡፡ ሹፌሩ የተሳፈሩበትን ሒሳብ እንዲከፍሉ ጠየቃቸው፡፡ ላም የራሷን ሒሳብ ከፈለች፡፡

2

ውሻም ከመሳፈሪያው በላይ ጨምሮ ከፈለ፡፡ ምክንያቱም የያዘው ገንዘብ እውነተኛ አልነበረም፡፡

3

ሹፌሩ የውሻውን መልስ ለመስጠት ተዘጋጀ፡፡ ፍየል በድንገት ወርዳ ሳትከፍል ሮጠች፡፡

4

ሹፌሩ በጣም ተናደደ፡፡ ለውሻው መልሱን ሳይሰጠው በታክሲው አመለጠ፡፡

5

ውሻ መልሱን ያስቀረበትን ሹፌር በመፈለግ ላይ ነው፡፡ ለዚያም ነው፣ ዛሬም ቢሆን መኪና ሲመጣ ወደ ውስጡ ለማየት እየሮጠ የሚከተለው፡፡

6

ፍየል መሳፈሪያ ባለመክፈሏ በእዳ እያዛለሁ ብላ ትፈራለች፡፡ የመኪና ድምጽ ስትሰማም ትሸሻለች፡፡

7

ላም መሳፈሪያዋን በሙሉ እንደከፈለች ታወቃለች፡፡ በመኪና አትረበሽም፡፡ መንገዱን ስታቋርጥም በዝግታ ትራመዳለች፡፡

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ፍየል፣ ውሻና ላም
Author - Fabian Wakholi
Translation - Kebede Yimer
Illustration - Marleen Visser
Language - Amharic
Level - First sentences