ዛማ ጎበዝ ነች
Michael Oguttu
Vusi Malindi

ታናሽ ወንድሜ ከእንቅልፉ ለመነሳት ይዘገያል።

እኔ ጎበዝ ስለሆንኩ ቀደም ብዬ እነቃለሁ!

1

ፀሐይዋን ወደ ቤት የማስገባት እኔ ነኝ፡፡

2

‹‹የንጋት ኮከቤ ነሽ›› ትለኛለች እማማ፡፡

3

በየቀኑ ራሴን በራሴ እታጠባለሁ፣ የማንንም እገዛ አልፈልግም፡፡

4

በቀዝቃዛ ውሃ ወይም ልብስ በሚታጠብበት በሰማያዊው ሳሙና ብታጠብ ግድ የለኝም፡፡

5

እማማ ‹‹ጥርሶችሽን አትርሺ›› ስትል ታስታውሰኛለች፡፡

እኔም ‹‹በጭራሽ፣ አልረሳም!›› በማለት እመልሳለሁ፡፡

6

ከታጠበኩ በኋላ አያቴ እና አክስቴን ሰላም እላለሁ፡፡

መልካም ቀንን እመኝላቸዋለሁ፡፡

7

ከዚያ ልብሴን እለብሳለሁ፡፡

‹‹አሁን ትልቅ ነኝ፣ እማማ›› እላለሁ፡፡

8

አዝራሮቼን መቆለፍና ጫማዬን ማሰር እችላለሁ፡፡

9

የትምህርት ቤት መረጃ ሁሉ ለወንድሜ እንደደረሰው አረጋግጣለሁ፡፡

10

በክፍል ውስጥ የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ፡፡

11

በየቀኑ እነዚህን ሁሉ ጥሩ ነገሮች አደርጋለሁ፡፡
በጣም የምወደው ነገር ግን አብዝቼ መጫወት ነው!

12
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ዛማ ጎበዝ ነች
Author - Michael Oguttu
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Vusi Malindi
Language - Amharic
Level - First sentences