ውሣኔ
Ursula Nafula
Vusi Malindi

መንደሬ ብዙ ችግር ነበረባት። ውሃ ከቦኖ ለመቅዳት ረጅም ሰልፍ እንሰለፍ ነበር።

1

በሌሎች ሰዎች የሚሰጠንን ምግብ እንጠብቅ ነበር።

2

ሌባ ፍራቻ ቤቶቻችንን በጊዜ እንዘጋ ነበር።

3

ብዙ ልጆች ትምህርታቸውን ያቋርጡ ነበር።

4

ወጣት ሴቶች በሌሎች መንደሮች ውስጥ በሰራተኝነት ያገለግሉ ነበር።

5

ግማሾቹ ወንዶች ልጆች በየሰፈሩ እየዞሩ ሲውሉ፤ ሌሎቹ ደግሞ በሰው ማሳ ላይ ያገለግሉ ነበር።

6

ነፋስ በነፈሰ ቁጥር ቆሻሻ ወረቀት በየአጥሩና በየዛፉ ላይ ይንጠለጠል ነበር።

7

ሰዎችን በጥንቃቄ ጉድለት የተጣለ ብርጭቆ ይቆርጣቸው ነበር።

8

አንድ ቀን ውሃው ቆመና የውሃ መያዣዎቻችን ባዶ ቀሩ።

9

አባቴ ሰዎች በመንደር ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ለመቀስቀስ ከቤት ቤት ዞረ።

10

ሰዎች ከአንድ ትልቅ ዛፍ ስር ተቀምጠው ያዳምጡ ጀመር።

11

አባቴ ተነስቶ ‹‹እነዚህን ችግሮቻችንን ለመፍታት በጋራ መስራት ይኖርብናል›› አለ።

12

ግንድ ላይ የተቀመጠው የስምንት ዓመቱ ዓመቱ ጁማ ‹‹እኔ በማጽዳት እራዳለሁ›› ሲል ተናገረ።

13

አንዲት ሴትዮም ‹‹ሴቶቹ ከኔ ጋር ዝሪት ላይ መሰማራት ይችላሉ›› አሉ።

14

ሌላ ሰውዬ ተነሳና ‹‹እኛ ወንዶቹ ጉድጓድ መቆፈር እንችላለን›› አለ።

15

ሁላችንም በአንድ ድምጽ ‹‹ህይወታችንን መቀየር ይኖርብናል›› በማለት ጮህን። ከዚያች ቀን ጀምረን ችግሮቻችንን ለመፍታት አብረን እንሰራ ጀመር።

16
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ውሣኔ
Author - Ursula Nafula
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Vusi Malindi
Language - Amharic
Level - First paragraphs