አናንሲና ጥበብ
Ghanaian folktale
Wiehan de Jager

በድሮ ዘመን ሰዎች ምንም አያውቁም ነበር። ሰብል እንዴት እንደሚዘራ፣ ሽመናም ሆነ የአንጥረኝነት ስራ እንዴት እንደሚሰራ ምንም ሃሳብ አልነበራቸውም። ንያሜ የተባለው በሰማይ ያለው አምላክ ግን የዓለምን ሁሉ ጥበብ ይዞ ነበር። በአንድ ገንቦም ውስጥ በጥንቃቄ  አስቀምጦት ነበር።

1

ከዕለታት አንድ ቀን ንያሜ ይህን የዕውቀት ገምቦ ለአናንሲ ለመስጠት ወሰነ። አናንሲ
የሸክላውን ገንቦ ባየ ቁጥር አንድ አዲስ ነገር ያገኝ ነበር። አጋጣሚው ያስደስት ነበር!

2

ገብጋባው አናንሲ ‹‹ይህን ገንቦ በአንድ ትልቅ ዛፍ ጫፍ በጥንቃቄ አስቀምጠዋለሁ። ከዚያም ሁሉም የኔው ይሆንልኛል!›› ሲል አሰበ። አንድ ረጅም ክርም ገምዶ በሸክላው ገንቦ ዙሪያ አሰረ፤ ከዚያም በሆዱ ዙሪያ ጠመጠመ። ዛፉንም መውጣት ጀመረ። ገንቦው አሁንም አሁንም ጉልበት ጉልበቱን እየመታው ዛፍ መውጣቱ ከበደው።

3

ይህን ሁሉ ጊዜም የአናንሲ ትንሽ ልጅ ከዛፉ ስር ቆሞ እየተከታተለው ነበር። እሱም ‹‹አዝለኸው ብትወጣ አይሻልም ወይ?››አለው።

አናንሲ ጥበብ የያዘውን የሸክላ ገንቦ ከጀርባው ለማሰር ሞከረ፤ እውነትም አመቺ ነበር።

4

ባጭር ጊዜም ከዛፉ ጫፍ ደረሰ። እዚያም ቆም አለና ‹‹ይህ ሁሉ ዕውቀት የኔ እንዲሆን ነው የተፈለገው፤ ግን ይሄው ልጄ ከኔ የበለጠ ብልህ ሆነ!›› በማለት አሰበ።
አናንሲ በዚህ በጣም ተናዶ  ያንን የሸክላ ገንቦ ከዛፉ ላይ ወደ ታች ወረወረው።

5

መሬትም ላይ ወድቆ ፍርክስክሱ ወጣ። ጥበብም ለማንኛውም ሰው በእኩል ተዳረሰ።
በዚህም ምክንያት ነበር ሰዎች እርሻ፣ ሽመና፣ አንጥረኝነትና ሌሎችንም ሰዎች መስራት የሚችሏቸውን ነገሮች ሁሉ የተማሩት።

6
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
አናንሲና ጥበብ
Author - Ghanaian folktale
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Wiehan de Jager
Language - Amharic
Level - First paragraphs