አይጦችና ድመቶች
Merga Debelo
Jacob Kono

በጥንት ዘመን ድመቶችና አይጦች ጓደኛማቾች ነበሩ፡፡

1

ከጊዜ በኋላ አይጦቹ ዘመዶቻቸውን እያጡ ሄዱ፡፡

2

አንድ ሽማግሌ አይጥ እንዲህ አለ፣ “ድመቶቹ እኛን እየበሉን ነው”፡፡

3

እናት አይጦችም ልጆቻቸውን፣ "ተጠንቀቁ! በፍጹም ወደ ውጪ እንዳትወጡ" ሲሉ መከሩ፡፡

4

ሁሉም አይጦች ጥንቃቄ አደረጉ፡፡ በየጉድጓዶቻቸውም አድፍጠው ተቀመጡ፡፡

5

የተራቡ አይጦች መጠየቅ ጀመሩ፣ “አይጦቹ ሁሉ የት ገቡ?”

6

ድመቶቹ አይጦቹን ለመጎብኘት ብሎም በጋብቻ ለመዛመድ ወሰኑ፡፡

7

እነሱም፣ "በሉ ከሴት ልጆቻችሁ አንዷ ወንድ ልጃችንን ታግባ" አሏቸው አይጦቹን፡፡

8

አይጦቹም መልሰው ድመቶቹን፣ "አረ! ልትበሉን ፈልጋችሁ ነው አይደል?" አሏቸው፡፡

9

ከጊዜ በኋላ አይጦቹና ድመቶቹ ልጆቻቸውን ሊያጋቡ ተስማሙ፡፡

10

ከዚያም ድመቶቹ ከንፈራቸውን በምላሳቸው እየላሱ በደስታ ወደቤታቸው ተመለሱ፡፡

11

በሰርጉ ቀን አይጦቹ ጥንቁቅ ነበሩ፡፡

12

ድመቶቹ ደግሞ የሰርግ ዘፈን እየዘፈኑ ደረሱ፡፡

13

ዘፈናቸውም፣ “ያዝ እጇን፣ ዝጋ ደጇን፣ ብላት አይጧን” የሚል ነበር፡፡

14

አንድ ሽማግሌ አይጥ በበኩላቸው እንዲህ ብለው ዘፈኑ፣ “ሩጥ ዘረ አይጥ! ሩጥ ካለህበት አምልጥ!”

15

ሽማግሌው አይጥም ድመቶቹን፣ “ጓደኞች አይደለንም” አሏቸው፡፡

16
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
አይጦችና ድመቶች
Author - Merga Debelo, Elizabeth Laird
Translation - Dawit Girma
Illustration - Jacob Kono
Language - Amharic
Level - First words