አያቴ፣ ጥንቸልና ዝሆን
Mutai Chepkoech
Marleen Visser

አያቴ እንደነገረችኝ፣ “ጥንቸልና ዝሆን ጎረቤታሞችና ጓደኞች ነበሩ፡፡”

1

ጥንቸሉ እንጉዳይ ይወዳል፤ ነገር ግን በጣም ሰነፍ ከመሆኑ የተነሳ ማምረት አይወድም፡፡

2

ምንም ዓይነት እንጉዳይ አልነበረም፡፡ በመሆኑም ጥንቸሉ የዝሆኑን ሙዝ መስረቅ ጀመረ፡፡

3

ዝሆኑ ይዝት ጀመር፣ "ሌባውን እይዘዋለሁ!" በማለት፡፡ ጥንቸል በጣም ፈራ፡፡

4

ዝንጀሮ ማሳውን ይጠብቅ ጀመር፡፡ ነገር ግን በዚያን ሰዓት ጥንቸል ሊሰርቅ አልመጣም፡፡

5

ዝሆኑ ማሳውን ሊጎበኝ ወጣ፡፡ ጥንቸሉም በዱባ ቅጠል ውስጥ ተደበቀ፡፡

6

ዝሆኑ ሁሉም ቦታ እየተዘዋወረ ያስስ ጀመር፡፡ ነገር ግን ሌባውን ሊይዘው አልቻለም፡፡

7

በሌላ ቀን፣ ጥንቸሉ በአንድ ትልቅ የዱባ ፍሬ ውስጥ ገብቶ ተደበቀ፡፡

8

ዝሆኑ ትልቅ የዱባ ፍሬ ተመለከተ ከዚያም ዋጠው፡፡

9

ዱባው በዝሆኑ ሆድ ውስጥ መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡

10

ከዚያም ዝሆኑ ዱባውን ተፋው፡፡ ጥንቸሉም ተፈትልኮ አመለጠ፡፡

11

አያቴም አለች፣ “ተረቴን መልሱ አፌን በዳቦ አብሱ”

12
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
አያቴ፣ ጥንቸልና ዝሆን
Author - Mutai Chepkoech
Translation - Dawit Girma
Illustration - Marleen Visser
Language - Amharic
Level - First words