መምህሬ
Zimbili Dlamini
Jesse Pietersen

መምህሬን በጣም እወዳታለሁ፡፡

1

እሷ በጣም ጥሩ መምህርት ነች፡፡ በጣምም ደግና ታጋሽ መምህርት ነች፡፡

2

ፀጉሯንም ጥሩ አድርጋ ነው ጉንጉን የምትሰራው፡፡

3

ፀጉሯ ላይም በቀለማት የደመቁ ዶቃዎችን ታደርጋለች፡፡

4

ዶቃዎቹም አረንጓዴ ፣ነጭ፣ቀይ እና ቢጫ ናቸው፡፡

5

"እማዬ የኔንም ፀጉር እንደ መምህሬ ስሪኝ?"

6

ትልቅ ስሆን ደግሞ ፀጉሮቼ ላይ ዶቃዎችን አደርጋለሁ፡፡

7

ሳድግ ደግሞ ልክ እንደ መምህሬ ጥሩ ሰው መሆን ነው የምፈልገው፡፡

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
መምህሬ
Author - Zimbili Dlamini, Hlengiwe Zondi
Translation - ፋሲል አሠፋ (Fasil Assefa), ፋሲል አሠፋ (Fasil Assefa)
Illustration - Jesse Pietersen
Language - Amharic
Level - First words