ዝሆንን ያታለለችው ጥንቸል
Agnes Gichaba
Wiehan de Jager

ጥንቸልና ዝሆን ጥሩ ጓደኛሞች ነበሩ፡፡

1

እንስሳዎቻቸውንም የግጦሽ መሬትና ውኃ ወዳለበት ስፍራ ወሰዷቸው፡፡

2

ኳስ መጫወትም በጣም ይወዱ ነበር፡፡

3

በጨወታውም ዝሆን ብዙ ጎል አስቆጠረ፤ በዚህ ጊዜ ጥንቸል ተከፋች፡፡

4

‹‹እንዴት ነው ግን እንደዚህ ጎበዝ ተጫዋች መሆን የቻልከው?›› በማለት ጥንቸል ዝሆንን ጠየቀችው፡፡ ‹‹ረጃጅም እግሮቼ ናቸው ጎበዝ ያደረጉኝ›› አላት፡፡

5

በሩጫ ስታሸንፈው ዝሆንም በተራው ተከፋ፤ ጥንቸልንም ‹‹እንዴት ነው ግን ጥሩ ሯጭ የሆንሽው?›› ብሎ ጠየቃት፡፡ ጥንቸልም ‹‹ቀጫጭን እግሮቼ ናቸው ጥሩ ሯጭ ያደረጉኝ›› ስትል መለሰች፡፡

6

ዝሆንም ‹‹እግሮቼን እንዳንቺ እንዴት ቀጭን ማድረግ እችላለሁ?›› ሲል ለጥንቸል ጥያቄ አቀረበ፡፡ ጥንቸልም ‹‹እንዴት እንደሆነ አሳይሃለሁ›› በማለት መለሰችለት፡፡

7

ከዚያም ጥንቸሏ በአካባቢው ወደሚገኝ የሚነድ እሳት ዝሆንን ወሰደችውና ‹‹በል እሳቱ ላይ ውጣና ቁም፡፡ ከዚያም እግሮችህ እንደኔ ቀጫጭን ይሆኑልሃል” ስትል ነገረችው፡፡ ዝሆንም እሳቱ ላይ ወጥቶ ቆመ፡፡

8

ዝሆኑ ‹‹ተቃጠልኩ እኮ›› በማለት ጮኸ፡፡

9

ጥንቸልም “እግሮችህ እንዲቀጥኑልህ ከፈለክ ብቸኛው መንገድ ይሄ ስለሆነ ቻለው” በማለት ተናገረች፡፡

10

ዝሆንም ህመሙ ከአቅሙ በላይ ሲብስበት ከእሳቱ በሩጫ በመውጣት በጀርባው ተንጋለለ፡፡

11

ከዛ ቀንም ጀምሮ ዝሆን ለብዙ ቀናት ከወደቀበት ተነስቶ በእግሩ መቆም ሳይችል ቆየ፡፡

12

ከብዙ ቀናት በኋላ ህመሙ ሲያገግምለት ቀስ እያለ ወደ ቤተሰቦቹ ጋር ተመለሰ፡፡

13

ጥንቸልም የሰራችው ስራ ትክክል እንዳልሆነና ጥፋትም እንደሆነ በመገንዘብ በጣም ተፀፀተች፡፡ በጥፋቷም አፍራ ዝሆንን ይቅርታ እንዲያደርግላት ጠየቀች፡፡

14
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ዝሆንን ያታለለችው ጥንቸል
Author - Agnes Gichaba
Translation - ፋሲል አሠፋ (Fasil Assefa)
Illustration - Wiehan de Jager
Language - Amharic
Level - First sentences