እንስሳቱ እግር ተሰጣቸው
Mutugi Kamundi
Wiehan de Jager

ከረጅም ጊዜ በፊት እንስሳት እግር አልነበራቸውም፡፡

1

ማስረሻ እግር የሰጠው ለሰዎች ብቻ ነበር፡፡

2

ማስረሻ ለሁሉም እንስሳት እግር ሊሰጣቸው ወሰነ፡፡

3

እንስሳቱ ለመራመጃና ለመሮጫ እግር ያስፈልጋቸው ነበር፡፡

4

መንፏቀቅ ይቸግራቸው ነበር፡፡

5

ቀኑ ሲደርስ የተለያዩ እንስሳት ወደ ማስረሻ ቤት እየተንፏቀቁ ሄዱ፡፡

6

ማስረሻም ለእንስሳትና ለወፎች እግር ሰጣቸው፡፡

7

የተወሰኑ እንስሳት ሲጨፍሩ፤ ሌሎቹ ደግሞ ወደቁ፡፡

8

‹‹ከእንግዲህ አንንፏቀቅም›› አሉ፡፡

9

ሃምሳ እግር የተሰለፈው ከመጨረሻ ነበር፡፡

10

ማስረሻ የቀሩትን እግሮች ሁሉ ለሃምሳ እግር ሰጠው፡፡

11

ሃምሳ እግርም በደስታ ‹‹ከሌሎቹ ፈጥኜ መሄድ እችላለሁ›› አለ፡፡

12

ከሃምሳ እግር በኋላም እባብ ‹‹ለኔም እግር ስጠኝ›› በማለት እየለመነ መጣ፡፡

13

እባብ ለማስረሻ ‹‹እንቅልፍ ጥሎኝ እኮ ነው›› አለው፡፡

14

ማስረሻ ለእባብ ምንም እግር ሊያገኝለት አልቻለም፡፡

15

ከዚያን ቀን ጀምሮ እባብ እግር እንዲሰጠው ይጠባበቃል፡፡

16
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
እንስሳቱ እግር ተሰጣቸው
Author - Mutugi Kamundi
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Wiehan de Jager
Language - Amharic
Level - First words