ፋናና እንስሶቿ
Foziya Mohammed
Jesse Breytenbach

ፋናና ቤተሰቧ ህዝብ በሚበዛባት የኢትዮጵያዋ ደብረብርሃን ከተማ ይኖራሉ፡፡ ፋና የሦስተኛ ክፍል ተማሪ ናት፡፡ ቅንና ብልህ ናት፡፡

1

ፋና እንስሳትን ትወዳለች፡፡ አንዲት ድመት፣ ሁለት ዶሮች፣ አንድ ፍየል እና እርግብ አሏት፡፡ ከእነዚህ የቤት እንስሳት ጋር ስትመግባቸውና ስትጫወት ታሳልፋለች፡፡

2

አንድ ቀን ፋና ከጓደኞቿ ጋር በትምህርት ቤት ግቢ እየተጫወተች ሳለ ልጆች እርግቦቹ ላይ ድንጋይ ሲወረውሩባቸው አየች፡፡ ‹‹ለምንድነው እርግቦቹን የሚጎዷቸው?›› በማለት ራሷን ጠየቀች፡፡

3

ጨዋታዋን አቋርጣ ድንጋይ ወደሚወረውሩት ልጆች በኩል ሮጠች፡፡ በመጀመሪያ ጓደኞቿ ምን እንደተከሰተ አልገባቸውም ነበር፡፡ በኋላ ግን ተከተሏት፡፡‹‹ድንጋይ አትወርውሩ›› በማለት ፋና ጮኸች፡፡

4

ሌሎቹ ልጆች ሮጠው ጠፉ፡፡ ፋና የተጎዱትን እርግቦች ያዘቻቸው፡፡ ክንፎቻቸው ላይ እንደቆሰሉ አየች፡፡ ሁለቱን እርግቦች ወደ ቤቷ ወስዳ ለመንከባከብ ወሰነች፡፡

5

እርግቦቹን መገበቻቸው፡፡ ምሽትም ላይ ለቤተሰቧ ቀን ያየችውንና ያደረገችውን እንዲሁም እርግቦቹን እንዴት እንዳዳነቻቸው ተናገረች፡፡

6

ጠዋት ፋናና ቤተሰቧ ወደ ሐኪም ቤት ሄደው ለእርግቦቹ መድሃኒት ገዙላቸው፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ የእርግቦቹ ቁስል ዳነ፡፡ ፋና በጣም ተደሰተች፡፡

7

ፋና ሁልጊዜ ለጓደኞቿ ‹‹እኔ እንስሳትን እወዳለሁ፡፡ እንስሳት ለኛ ጠቃሚና ጓደኞቻችን ናቸው፡፡ ከጉዳት ልንጠብቃቸውና ልንንከባከባቸው ይገባናል›› በማለት ትናገራለች፡፡

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ፋናና እንስሶቿ
Author - Foziya Mohammed
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Jesse Breytenbach
Language - Amharic
Level - First paragraphs