ገንፎ
Zimbili Dlamini
Catherine Groenewald

አየለ ወደ  ትምህርት ቤት ለመሄድ እየተዘጋጀ ነው፡፡

1

አባት ለቁርስ ገንፎ እያዘጋጀ ነው፡፡

2

''እናቴ ምርጥ ገንፎ ትሰራለች!'' አለ አየለ፡፡.

3

ገንፎ ለአየለ ኃይል ሰጠው፡፡

4

ገንፎው ተዘጋጅቷል፡፡

5

አባቱ በፍቅር ወተቱን ቀዳለት፡፡

6

''አባቴ፣ ይህ ገንፎ ተጨማሪ ስኳር ያስፈልገዋል'' አለ አየለ፡፡.

7

አየለ ''የእናቴ ገንፎ ከአባቴ በጣም የተሻለ ነው'' ብሎ አሰበ፡፡.

8

''አባቴ፣ እባክህ ተጨማሪ ስኳር ማግኘት እችላለሁ?'' በማለት አየለ ጠየቀ፡፡.

9

ለአየለ አባቱ ተጨማሪ ስኳር አደረገለት፡፡

10

''ዋው! አባቴ! ገንፎዬ ውስጥ ጨው ጨመርክበት!''.

11

''አባቴ  መቼ ነው እናቴ እቤት የምትመጣው?''.

12
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ገንፎ
Author - Zimbili Dlamini, Hlengiwe Zondi
Translation - ሂሩት, መዘምር ግርማ
Illustration - Catherine Groenewald
Language - Amharic
Level - First sentences