አዲሴ - የእግር ኳስ ኮከቧ
Eden Daniels
Eden Daniels

አዲሴ ወንዶች ልጆች ኳስ ሲጫወቱ እየተመለከተች ነው፡፡ ከልጆቹ ጋር ተቀላቅላ መጫወት ፈለገች፡፡

1

አሰልጣኙንም ከልጆቹ ጋር እግር ኳስ ልምምድ መስራት ትችል እንደሆነ ጠየቀችው፡፡

2

አሰልጣኙ እጆቹን ወገቡ ላይ አደረገ፡፡ ''በዚህ ት/ቤት ወንድ ልጆች ብቻ ናቸው እንዲጫወቱ የተፈቀደላቸው'' አለ፡፡

3

ልጆቹ ሄዳ እጅ ኳስ እንድትጫወት ነገሯት፡፡ እነሱም ለሴት እጅ ኳስ እንደሆነ፤ እግር ኳስ ግን ለወንድ ልጆች እንደሆነ ነገሯት፡፡ አዲሴ ተናደደች፡፡

4

በሚቀጥለው ቀን ትምህርት ቤቱ ታላቅ የአግር ኳስ ግጥሚያ ነበረበት፡፡ አሰልጣኙ በጣም ተጨንቋል፡፡

5

ምክንያቱም የቡድኑ ወሳኝ ተጫዋች በሕመም ምክንያት መጫወት ባለመቻሉ ነበር፡፡

6

አዲሴ ወደ አሰልጣኙ እየሮጠች ሄዳ እንድትጫወት እንዲፈቅድላት ለመነችው፡፡ አሰልጣኙ ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ ገባው፡፡ ከዚያም አዲሴ ቡድኑን እንድትቀላቀል ፈቀደላት፡፡

7

ጨዋታው በጣም ፈታኝ ነበር፡፡ በመጀመሪያው ግማሽ የጨዋታው ክፍለ ጊዜ ማንም ጎል ሊያስቆጥር አልቻለም፡፡

8

በሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታው ጊዜ ከልጆቹ መካከል አንዱ ኳስ ለአዲሴ አቀበላት፡፡ ኳሱን በፍጥነት ወደ ጎል እያንከባለለች ሄደች፡፡ ከዚያም ኳሱን በኃይል አክርራ መታችውና ጎል አስቆተረች፡፡

9

ተመልካቹ በደስታ አበደ፡፡ ከዚያም ቀን ጀምሮ ሴቶች በትምህርት ቤቱ  ኳስ እንዲጫወቱ ተፈቀደላቸው፡፡

10
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
አዲሴ - የእግር ኳስ ኮከቧ
Author - Eden Daniels
Translation - ዳዊት ግርማ, መዘምር ግርማ
Illustration - Eden Daniels
Language - Amharic
Level - First sentences