ሌባው ልጅ
መንበረ ፍቃደ
መንበረ ፍቃደ

ከእለታት አንድ ቀን ሁለት ጓደኛሞች ነበሩ።

1

ስማቸውም መስፍ እና ንጉስ ይባላል።አንድ ቀን መስፍን እንደልማዱ ወደ ትምህርት ቤት መጣ።

2

ጓደኛውን ንጉስን እንዲህ ሲል ጠየቀው።የተማሪዎቹን የመማሪያ ቁሳቁስ ዕንስረቃቸው አለ።ንጉስም ተው ይሄተግባር አያዋጣንም አለው።መስፍንም አይሆንም አይሆንም!!!ዛሬማ መስረቅ አለብኝ ሲል መለሰለት።ንጉስም ተው ይሄ ስራ ያስቀጣሀል አለው።መስፍንም መስረቅህ ያስከብርሀል እንጂኮ አይጎዳሕም በማለት ወደክፍሉ ገባ።

3

በአንደኛው ክፍለ ጊዜ አማረኛ ትምህርት ስለነበራቸው ስለዕለቱ ትምህርት ካስረዳች ቡሀላ የክፍል ስራ ሰጠች።መስፍን ግን የክፍሉን ስራ መስራቱን ትቶ አብራው የምትቀመጠውን የሳራን ቦርሳ በአይኑ የምርምር ጀመረ።ሳራም የክፍሉን ስራ ልታሳርም ወደመምህሯ ሄደች።ቀስ በማለት ውድ ቦርሳው እጅን ሰደደ።

4

ውይይት እንደ ድንገት ስር ዞር ስትል መስፍን ከቦርሳዋ ማስመሪያ ሲያወጣ አየችው።ሳራም ድንግጥ አስቀምጥ አስቀምጥ!!!እያለች ጮኸች።ተማሪዎቹ ሁሉ ወደ መስፍን አፈጠጡ።

5

መምህሯም መስፍንን ወደ ቢሮ ወሰደችው እርእሰ መምህሩም እንዲህ ዐለው በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ሲሰጥህ ነበር።ነገርግን ከስህተትህ ልትማር አልቻልክም ስለዚህ ከትምህርት ቤቱ ተባረሀል አለው።ጓደኞቹ ሁሉ አዘኑበት፣እሱም ስርቆት ያዋጣኛል ብሎ ሲጎርር የነበረውና የጓደኛውን ምክር አለመስማቱ ፀፀተው።እጣፈንታውም ከትምሕርት መባረር ሆነና ቀረ።

6
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ሌባው ልጅ
Author - መንበረ ፍቃደ
Illustration - መንበረ ፍቃደ
Language - Amharic
Level - First paragraphs